ማንችስተር ዩናይትድ በብራይተን ተሸንፎ ከካራባኦ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነ

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድ በብራይተን ተሸንፎ ከካራባኦ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነ

AMN-መስከረም 6/2019 ዓ.ም

ማንችስተር ዩናይትድ በ3ኛ ዙር የካራባኦ ካፕ ጨዋታ ብራይተንን አስተናግዶ 3ለ2 ተሸንፏል።

በኦልድትራፎርድ በተደረገው ጨዋታ ዩናይትድ በሼ ሌሲ እና ሜሰን ማውንት ግቦች 2ለ0 መምራት ችሎ ነበር።

አስደናቂ ብቃት ያሳየው ብራይተን ካራላምቦስ ኮስቱላስ ፣ ፓስካል ግሮስ እና ማርቲን ዴ ካይፐር ባስቆጠሯቸው ግቦች ውጤቱን ቀልብሶ 3ለ2 አሸንፏል።

በሳምንቱ መጨረሻ በሊጉ የደርቢ ጨዋታ በማንችስተር ሲቲ የተሸነፈው ዩናይትድ ገና በ3ኛው ዙር ከካራባኦ ካፕ ውድድር ውጪ ሆኗል።

በኦልድትራፎርድ የታደሙ ተመልካቾችም ቡድኑ ባሳየው ብቃት ባለመደሰት የተቃውሞ ድምፅ አሰምተዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች አስቶን ቪላ ኮቬንትሪ ሲቲን 3ለ1 ፣ ኤቨርተን ዎልቭስን 1ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review