አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና ሀገሬ ቴሌቪዥን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና ሀገሬ ቴሌቪዥን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

AMN- መስከረም 9/2019 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከሀገሬ ቴሌቭዥን ጋር በመተባበር የቀጥታ ስርጭት ሽፋን በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት አድርገዋል።

ስምምነቱን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ እና የሀገሬ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንዋይ ይመር ተፈራርመዋል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በቀጥታ ስርጭት የላቀ ልምድ አካብቷል ያሉት አቶ ሰለምን ዲባባ በጋራ ሰርተን ለማህበረሰቡ የተሻለ መረጃ ተደራሽ በማድረግ አዎንታዊ ተጽእኖ መፍጠር እንችላለን ብለዋል።

አቶ ንዋይ ይመር በበኩላቸው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የደረጀ የቴክኖሎጂ አቅም እና የሰው ሀይል ያለው በመሆኑ በጋራ ሰርተን የተሻለ ውጤት እናመጣለን የሚል ተስፋ አለን ሲሉ ተናግረዋል።

ተቋሙ ከእኛ ጋር ለመስራት ላሳየው ቀና ትብብር ምስጋናችንን እናቀርባለን ሲሉም አክለዋል።

ሀለቱ ተቋማት በፈጠሩት ትብብር ምክንያት በኮፐንሃገን የሚካሄደውን የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ውድድር በቀጥታ በማስተላለፍ ጀምረዋል።

በበላይነህ ይልማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review