ኢትዮጵያ የምታገኘውን የልማት ፋይናንስ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ለማዋል ያላትን ቁርጠኝነት ገለጸች

AMN – ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካለኝ (ዶ/ር) «በብዛትና በጥራት የተሻሉ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር አፈጻጸምን ማፋጠን» በሚል ርዕስ በተካሄደው የልዩ ሚኒስትሮች ውይይት ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ገዥው በውይይቱ ወቅት፤ ኢትዮጵያ የምታገኘውን የልማት ፋይናንስ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ዕድሎች የመቀየር ቁርጠኝነቷን አጉልተው አሳይተዋል።

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር ያላትን አጋርነት መሠረት በማድረግ ማብራሪያ የሰጡት ኢዮብ (ዶ/ር)፤ የልማት ውጤቶችን ለማፋጠን የፕሮጀክቶችን ዝግጁነት ማሻሻል፣ የትግበራ ሂደቶችን ማቃለል እና የተቋማትን አቅም ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አክለውም የልማት ፋይናንስ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ድህነትን በመቀነስና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማረጋገጥ ረገድ ትርጉም ያለው ውጤት እንዲያስገኝ፤ ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር በቅርበት ለመስራት ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ያረጋገጡ መሆኑን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተገኘው መረጃ ያመላክታል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review