AMN – ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም

በከተማዋ የደንብ መተላለፍ 77 በመቶ መቀነሱን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው::

የባለሥልጣኑ ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለጹት፣ ተቋሙ በሩብ ዓመቱ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ ተወጥቷል።
በተለይም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራርን በመተግበሩ ምክንያት በከተማዋ የሕግ ማስከበር ሥራው ውጤታማ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል።
ሥራ አስኪያጁ አክለውም በከተማዋ ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ሙሉ በሙሉ መግታት ተችሏል ብለዋል።
ይህም የደንብ መተላለፍ ምጣኔው 77 በመቶ እንዲቀንስ ማስቻሉን አብራርተዋል።

ባለሥልጣኑ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ የተናገሩት ሻለቃ ዘሪሁን፣ የዓቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስና የደም ልገሳ መርሃ ግብሮችን በማካሄድ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን ማረጋገጡን ገልጸዋል።
በቴዎድሮስ ይሳ