AMN-ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 7ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬም ሲቀጥል ሊድስ ዩናይትድን ከማንችስተር ዩናይትድ የሚያገናኘው ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።
ማንችስተር ዩናይትድ አጀማመሩ አልሰመረለትም። አሰልጣኙ ማይክል ካሪክ ከስድስት የሊግ ጨዋታ አንዱን ብቻ ማሸነፉ ቆይታው ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል።
ዩናይትድ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች አራት ሽንፈት ገጥሞታል። በክለቡ ታሪክ መጥፎ ውጤት ተብሎም ተመዝግቧል።
ዛሬ ቀን 10:00 ከሜዳው ውጪ ሊድስን የሚያስተናግድበት ጨዋታም ፈታኝ ይሆንበታል ተብሎ ተገምቷል።

ሊድስ ያለፈው ሳምንት በአርሰናል እስኪረታ ድረስ በሊጉ ሽንፈት አልገጠመውም ነበር። በተለይ በሜዳው ፈታኝ ቡድን እንደሆነ ደጋግሞ አሳይቷል።
በጨዋታው በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ፓትሪክ ዶርጉ እና ቤንጃሚን ሼሽኮ በጉዳት የማይሰለፉ ተጨዋቾች ናቸው ፤ የሉክ ሾው እና ኮቢ ማይኖ መሳተፍም አልተረጋገጠም።
ሊድስ ዩናይትድ ከስድስት ጨዋታ ዘጠኝ ነጥብ በመያዝ 8ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፣ ስድስት ነጥብ ያለው ማንችስተር ዩናይትድ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዛሬ በሚደረግ ሌላ ጨዋታ ያለፈው ዓመት የሊጉ አሸናፊ አርሰናል ወደ ሲቲ ግራውንድ አቅንቶ ኖቲንግሀም ፎረስትን ይገጥማል።

አርሰናል ያደረጋቸውን ሰባቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ በ21 ነጥብ ሊጉን ከሚመራው ማንችስተር ሲቲ ላለመራቅ ድሉ ያስፈልገዋል።
ምሽት 12:30 በሚጀምረው ጨዋታ በአርሰናል በኩል ፒዬሮ ሂንካፒዬ እና ክሪስቶስ ዞሊስ አይሰለፉም። ማርቲን ዙቢሜንዲ ግን በስብስቡ ሊካተት ይችላል።
ብራይተን ከ ፓላስ ፤ ቦርንማውዝ ከ ሰንደርላንድ ዛሬ የሚደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ናቸው። ሁለቱም ጨዋታዎች 10:00 ሲል ይጀምራሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ