AMN- ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተለያዩ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያደረገችው የልማት እንቅስቃሴዎች፣ ሀገሪቱ ከአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌትነት አልፋ የነገውን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እያረጋገጠች መሆኑን እያስመሰከሩ ይገኛሉ።
የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አሻራ ከፍ ከሚያደርጉ እና የነገዋን የኢትዮጵያ ከፍታ ከሚያረጋግጡ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መካከል፤ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውለው የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም እና የቦሌ ለሚ ዘመናዊ የወርቅ ማጣሪያ ማዕከል በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።
እነዚህ መሠረታዊ የልማት ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ገጽታ በመቀየር ረገድ እጅግ የላቀ አበርክቶ የሚኖራቸው ሲሆን፤ ኢትዮጵያን በአፍሪካ የኢኮኖሚ፣ የቱሪዝም፣ የኢንዱስትሪ እና የቴክኖሎጂ ማዕከል እንደሚያደርጓት ይታመናል።
በሌላ መልኩ በኃይል አቅርቦትና በሉዓላዊ የኢኮኖሚ ምሰሶነት ከሚጠቀሱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሲሆን፣ ለነገዋ ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ አብዮት እውን መሆን ዋና የጀርባ አጥንት ሆኖ እንዲያገለግል ከፍተኛ እምነት ተጥሎበታልታል።
በሳይንስና ቴክኖሎጂው ዘርፍ የኒውክሌር መሠረተ ልማት ግንባታ፣ የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ አቅም ከፍታ ከማድረጉም በላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የላቀ የኃይል ማዕከል እንድትሆን ያስችላታል።
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ኃይልን፣ ለሕክምና እና ግብርናን ለማዘመን የምታደርገው ጥረት ለነገው ትልቅ ተስፋን የሚፈነጥቅ ሲሆን፤ ይህም ሀገሪቱን በሳይንሳዊ ዕውቀት የሚያበለጽግላት ነው።

በማዕድን ዘርፍ እየተመዘገቡ ያሉ አስደናቂ ስኬቶችም የኢኮኖሚውን አውድ እያጠናከሩት ይገኛሉ።
ጥራቱን የጠበቀ ወርቅ በሀገር ውስጥ በማጣራት ለዓለም አቀፍ ገበያ ማቅረብ መቻሉ፤ የኢትዮጵያን የንግድ ተወዳዳሪነት ከማሳደጉም በላይ የውጭ ጥገኝነትን በሰበረ መልኩ ራስን በራስ የመቻል ማሳያ የሆነ ትልቅ ምዕራፍ ነው።
ግዙፍ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የለሙ መሬቶች በቴክኖሎጂ በመታገዛቸው ምርትና ምርታማነት በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ አድጓል። ይህ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ቁርኝት የነገዋን ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋ ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
እነዚህ ሁሉ ታላላቅ የልማት እንቅስቃሴዎች ተቀናጅተው ሲሠሩ፤ ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የብልጽግናዋን ከፍታ የሚያረጋግጥ ነው።
በወርቅነህ አቢዮ