AMN- ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን በታላቁ የክሬምሊን ቤተ-መንግሥት አቀባበል አድርገዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን በሞስኮ እየተካሄደ ያለውን 3ኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ አስመልክቶ በታላቁ የክሬምሊን ቤተ መንግሥት በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ መቀበላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።