ብራይተን ማንችስተር ሲቲን አሸነፈ

You are currently viewing ብራይተን ማንችስተር ሲቲን አሸነፈ

AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም

በሜዳው ኢትሃድ ስታዲየም ብራይተንን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ 1ለ0 ተሸንፏል።

ስዊድናዊው አማካይ ያሲን አያሪ የብራይተንን የማሸነፊያ ግብ 11ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

የውድድር ዓመቱን በአስደናቂ ብቃት የጀመረው ብራይተን ከዘጠኝ የሊጉ ጨዋታዎች 19 ነጥብ ሰብስቦ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በሊጉ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን የተሸነፈው ማንችስተር ሲቲ በ21 ነጥብ ለጊዜው በመሪነቱ ቀጥሏል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች ቦርንማውዝ ሊድስ ዩናይትድን 2ለ0 ፣ ኮቬንትሪ ሲቲ ሰንደርላንድን 3ለ1 ፣ ብሬንትፎርድ ናቲንግሃምን ፎረስትን 2ለ0 ሲያሸንፉ ፤ ኢፕስዊች እና ሀል ሲቲን 2ለ2 ተለያይተዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

#AMNSport

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review