በመደመር ፍልስፍናችን እየተመራን የአየር ንብረት ተስማሚ መፍትሄዎችን በስፋት እያሳደግን እንገኛለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing በመደመር ፍልስፍናችን እየተመራን የአየር ንብረት ተስማሚ መፍትሄዎችን በስፋት እያሳደግን እንገኛለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ኅዳር 2/2019 ዓ.ም

በመደመር ፍልስፍናችን እየተመራን የአየር ንብረት ተስማሚ መፍትሄዎችን በስፋት እያሳደግን እንገኛለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት የቱርክዬ መንግሥትና ሕዝብ ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል፣ እንዲሁም ድርድሩን ለምትመራው አውስትራሊያ የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

‎ለኢትዮጵያ የአየር ንብረት እርምጃ፤ የዜጎችን የእለት ተእለት ኑሮ ለማሻሻል፣ የመቋቋም አቅምን ለማጠናከር እና የተመዘገቡ የልማት ስኬቶችን ዘላቂ ለማድረግ እጅግ ወሳኝ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲያችን አካል ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በመደመር ፍልስፍናችን እየተመራን፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብራችን እስካሁን ከ56 ቢሊየን በላይ ችግኞችን መትከል የቻልን ሲሆን፣ በተመሳሳይ መልኩ የታዳሽ ኃይል ልማትን፣ ዘላቂ የከተማ ግንባታን እና የአየር ንብረት ተስማሚ መፍትሄዎችን በስፋት እያሳደግን እንገኛለን ብለዋል፡፡

‎አሁን ላይ ከቃል ኪዳን ባለፈ ወደ ፈጣን ተግባራዊ እርምጃዎች መሸጋገር ይኖርብናል፤ ይህም በቀላሉ ሊገኝ በሚችል የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ይበልጥ ጠንካራ በሆኑ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች እና ተጋላጭ ለሆኑ ማህበረሰቦች የመቋቋም አቅም ግንባታ ላይ በሚደረግ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተግባራዊ መደረግ አለበትም ነው ያሉት።

‎ኢትዮጵያ መጪውን የCOP32 ፕሬዚዳንትነት ስትረከብ እነዚህን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በግንባር ቀደምትነት የምታራምድ ሲሆን፣ ስኬታማ ውጤት እንዲመዘገብም ከCOP31 ፕሬዝዳንት ጋር በቅርበትና በትብብር ትሠራለች ብለዋል።

እንዲሁም መላውን ዓለም ለCOP32 ጉባኤ ወደ ምድረ ቀደምት ሀገር ወደሆነችው ኢትዮጵያ ለመቀበል ዝግጁ ነን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review