ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአፍሪካ የድርድር ቡድን (AGN) ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአፍሪካ የድርድር ቡድን (AGN) ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

AMN- ኅዳር 2/2019 ዓ.ም

በኮፕ 31 አንታሊያ ከሚካሄዱ ዝግጅቶች ጎን ለጎን፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአፍሪካ የድርድር ቡድን (AGN) ሊቀመንበር አንትዊ-ቦአሲያኮ አሞአ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ ለአፍሪካ ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ማለትም የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ፍትሐዊ ሽግግር እና ትግበራን ላይ ያተኮረ ነበር።

በተጨማሪም ታዳጊ ሃገሮች በብሔራዊ የተወሰኑ አስተዋጽኦዎቻቸው (NDCs) እና በብሔራዊ የማጣጣሚያ ዕቅዶቻቸው (NAPs) ትግበራ የበለጠ ድጋፍ እንዲያገኙ እንዲሁም የአየር ንብረት እርምጃዎች የአፍሪካን የልማት ቅድሚያዎች እንዲመልሱ አስፈላጊነቱን ተወያይተዋል።

የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንቱ ለኮፕ 32 ዝግጅቶች እየተጠናከሩ በሚሄዱበት ወቅት ኢትዮጵያ ከAGN ጋር የቅርብ ምክክር እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በአንታልያ የተሳካ ውጤት ማስመዝገብ፣ በድርድሩ ሂደቱ ላይ ያለውን እምነት ማጠናከር እና ከቃል ኪዳኖች ወደ ተግባራዊ አፈጻጸም መሸጋገር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቅድሚያዎችና አመለካከቶች ወደ ኮፕ 32 በሚደረጉ ዝግጅቶችና ውይይቶች ሂደት በጥንካሬ እንዲንጸባረቁ ከAGN ጋር በቅርበት መሥራቷን ትቀጥላለች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review