AMN ህዳር 2/2019
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ጋር ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡
ውይይታችን የረጅም ጊዜ ግንኙነታችንን ይበልጥ ለማጠናከር እና የጋራ የመልማት አቅም ባላቸው ዘርፎች ላይ ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለመ ነበር ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልእክት አስተላልፈዋል፡፡