AMN ኅዳር 2/2019 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ከCOP31 መድረክ ጎን ለጎን፣ ከህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬት ሃምፕተን ጋር ገንቢ ውይይት አድርገናል አድርገናል ብለዋል፡፡
ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ሃምፕተን ጋር ኢትዮጵያ የCOP32 አዘጋጅ ሀገር እንደመሆኗ በትብብር ዕድሎች፣ እንዲሁም በቆሻሻ አያያዝና አጠቃቀም ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምና የከተሞች ትብብርን በማጠናከር ዙሪያ ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ዘላቂ፣ አረንጓዴና አካታች የከተማ ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ትብብር ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የተሻለችና ዘላቂ ከተማ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሠራለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡