የሕዝባችንን የቤት ጫና ማቃለል ለእኛ የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን አደራና ኃላፊነት በመሆኑ 24/7 ተግተን እንሰራለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የሕዝባችንን የቤት ጫና ማቃለል ለእኛ የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን አደራና ኃላፊነት በመሆኑ 24/7 ተግተን እንሰራለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ኅዳር 4/2019 ዓ.ም

የሕዝባችንን የቤት ጫና ማቃለል ለእኛ የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን አደራና ኃላፊነት በመሆኑ 24/7 ተግተን እንሰራለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቃልን በተግባር ! በሚል መሪቃል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከጉባ ብስራቶች አንዱ እንደ ሀገር በአምስት ዓመታት ውስጥ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለዜጎቻችን ለማስረከብ የገባነው ቃል ነው።

እንደ አዲስ አበባም በ21 ሳይቶች 100 ሺህ ቤቶችን እየገነባን ነው። እነዚህም 50 ሺህ በከተማው በጀት፣ 50 ሺህ ደግሞ በመንግሥት–የግል አጋርነትና በማኅበራት እየተገነቡ ነው ብለዋል፡፡

ዛሬም ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር በቱሉ ዲምቱ 33 ብሎኮችን እና በአዲስ ከተማ ቅጠል ተራ 9 ብሎኮችን ጎብኝተን ጥሩ አፈፃፀም ላይ መሆናቸውን ተመልክተናል ብለዋል፡፡

የሕዝባችንን የቤት ጫና ማቃለል ለእኛ የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን አደራና ኃላፊነት በመሆኑ 24/7 ተግተን እንሰራለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review