በወጣቶች ኦሊምፒክ አመርቂ ውጤት ያመጣው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

You are currently viewing በወጣቶች ኦሊምፒክ አመርቂ ውጤት ያመጣው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

AMN ኅዳር 5/2019

ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር የተዘጋጀው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ በሴኔጋል ዳካር ከጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ 5 የወርቅ እና 3 የብር በአጠቃላይ 8 ሜዳልያዎችን በማግኘት በቀዳሚነት አጠናቃለች።

የሀገራችንን ሰንደቅዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረገው ልዑክ ቡድን

ዛሬ አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በአቀባበል ስነ ስርአቱ ላይ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) ፥ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፥ እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በአልታየህ ኪዳኔ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review