ኢትዮጵያ ለኢጋድ መመስረቻ ስምምነት ስኬታማነት በቁርጠኝነት ትሰራለች

You are currently viewing ኢትዮጵያ ለኢጋድ መመስረቻ ስምምነት ስኬታማነት በቁርጠኝነት ትሰራለች

AMN ህዳር 8/2019

ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) መመስረቻ ስምምነት ተግባራዊነት እና ስኬታማነት በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ገለጸች።

ኢትዮጵያ ለኢጋድ አባል ሀገራት እና ለኢጋድ ሴክሬታሪያትን፣ የ2023ቱ የኢጋድ መመሥረቻ ስምምነት ከትናንት ጀምሮ ሥራ ላይ መዋሉን በማስመልከት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ይህ ታሪካዊ ምዕራፍ አባል ሀገራቱ በኢጋድ እና በቀጣናው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ያላቸውን የጋራ እምነት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር፣ አብሮነት እና አጋርነት ለማጠናከር የተያዘውን የጋራ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክቷል።

ኢጋድ 40ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን በሚያከብርበት በዚህ ወቅት፣ ስምምነቱ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት፣ የልማት ዕድል እና ብልጽግና እንዲሰፍን የአባል ለገራቱን የጋራ ምኞት እውን ለማድረግ የሚያስችል ጠንካራ የሕግ መሰረት እንደሚጥል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በዋና ፀሐፊው ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የሚመራው የኢጋድ ሴክሬታሪያት፣ ስምምነቱን እውን ለማድረግ በሂደቱ ሁሉ ላሳየው ቁርጠኝነት እና ጽናት አድናቆቷን ችራለች።

ስምምነቱ በውጤታማነት ተግባራዊ እንዲሆን የበኩሏን ሚና ለመወጣት ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነትም አረጋግጣለች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review