በዳካር የወጣቶች ኦሎምፒክ ለተሳተፉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች እና የልዑካን ቡድን አባላት የ30 ሚሊዮን ብር የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ

You are currently viewing በዳካር የወጣቶች ኦሎምፒክ ለተሳተፉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች እና የልዑካን ቡድን አባላት የ30 ሚሊዮን ብር የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ

AMN ኅዳር 8/2019

በዳካር የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች 1ኛ ደረጃን በመያዝ ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የእውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።

በዚህም በውድድሩ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ በማድረግ ብሔራዊ ኩራት ለሆነው ልዑካን ቡድን፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የ16 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷል።

በዚሁ የሽልማት መርሐ-ግብር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በጋራ በመሆን፣ በውድድሩ ለተሳተፉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ለልዑካን ቡድኑ አባላት በአጠቃላይ የ30.5 ሚሊዮን ብር የማበረታቻ ሽልማት አበርክተዋል።

በሽልማት ድልድሉ መሠረት በዳካሩ የወጣቶች ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ላስመዘገቡ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ1.5 ሚሊዮን ብር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ የብር ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው የ750 ሺህ ብር ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

ኢትዮጵያ በዳካር በተካሄደው የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር 5 የወርቅ እና 3 የብር በድምሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ አኩሪ ድል መጎናጸፏ ይታወቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review