ለቄራ አካባቢ ወጣቶች በገነባነው እና ለአገልግሎት ክፍት ባደረግነው አካታች ዘመናዊ የስፖርት ሜዳ የማስ ስፖርት አካሂደናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ለቄራ አካባቢ ወጣቶች በገነባነው እና ለአገልግሎት ክፍት ባደረግነው አካታች ዘመናዊ የስፖርት ሜዳ የማስ ስፖርት አካሂደናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ሚያዝያ 10/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ማለዳ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቄራ አካባቢ ወጣቶች በገነባነው እና ለአገልግሎት ክፍት ባደረግነው አካታች ዘመናዊ የስፖርት ሜዳ (የ46 ሜዳ) የማስ ስፖርት አካሂደናል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት አፍቃሪ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ፤ በከተማ ማዕከል ብቻ ሳይሆን በየሰፈሩ ወጣቶች በአካል የጠነከሩ፣ በአዕምሮ የዳበሩ እና የበቁ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሆነው ኢትዮጵያ በስፖርት ዘርፍ የያዘችውን ራዕይ የሚያሳኩ እንዲሆኑ በትጋት እና ከልብ ሰርተናል።

ለዘመናት የተዋረድንበትን እና አንገት ያስደፋንን ድህነትና ጉስቁልና ወደ ብልፅግና ለመቀየር 24/7 እየሰራን አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ መኖሪያ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እያደረግናት ነው ብለዋል፡፡

በዓለም ላይ ከታወቅንበት ስፖርት እንኳን ወደ ኋላ እየተመለስን የመጣንበትን ሁኔታ በቁጭት ከመሰረቱ ለመለወጥ ፓርቲያችን ብልጽግና የገባውን ቃል በተግባር እያከናወነ፣ የህዝብ ተጠቃሚነትን፣ ወገንተኝነትን እና የሀገር ክብርን የማላቅ ተግባርን በእውነት እየከወነ ያለ ፓርቲ ነው።

ስለሆነም፣ ብልፅግና ቃሉን ይጠብቃል፤ ቃሉን ይፈጽማል፤ ሕዝቡን የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ያደርጋል!

የኢትዮጵያን ብልጽግና ማስቆም የሚችል አንዳችም ምድራዊ ኃይል የለም!!

በመሆኑም፣ ወደ ኋላ ሳንመለከት የወደፊት ተስፋችንን በተጨባጭ ተግባር እያመላከትን ስኬታማ ጉዟችንን እናስቀጥላለን፤ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review