ለአረጋዊያን የሚደረገው ድጋፍ የአረጋዊያንን የልማት ተሳትፎ የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing ለአረጋዊያን የሚደረገው ድጋፍ የአረጋዊያንን የልማት ተሳትፎ የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገለጸ

AMN ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም

‎የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አረጋዊያን ዕድል ከተመቻቸላቸው መስራት ይችላሉ በሚል መሪ ቃል ለአረጋዊያን የገቢ ማስገኛ የሚውሉ ዶሮዎች፤ መኖ እና የዶሮ ኬጅ ድጋፍ አድርጓል።

‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ አረጋዊያን የሀገር ባለውለታ የታሪክ ድልድይና ክብር ናቸው ብለዋል።

‎በሴፍቲኔት መርሃ ግብር በህብረተሰብ ተሳትፎ የቤት እድሳት ድጋፍና በምገባ መርሃ ግብር የከተማ አስተዳደሩ አረጋዊያንን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ለአረጋዊያን የሚደረገው ድጋፍ አረጋዊያኑን ንቁና ውጤታማ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ አንደሚያደርግ ተናግረዋል።

‎የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸዉ መንግስት አረጋዊያን ሆነው መንቀሳቀስ ለሚችሉ ሰርተው ገቢ የሚያገኙበትን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ክፍለ ከተማውም ዶሮ ፤ መኖ እና ኬጅ መስጠቱን ተናግረዋል።

‎የአዲስ አበባ አረጋውያን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ክፍሉ መንግስት ለአረጋውያን እየሰጠ ያለው ትኩረትና ድጋፍ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።

‎ድጋፉ የተደረገላቸው አረጋዊያን በበኩላቸው አረጋዊያንን የሚያከብር ትውልድ ለራሱ ክብር የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል።

‎የተሰጣቸው የመስሪያ ድጋፍም አረጋዊያን መስራት እንደሚችሉ ማሳያ በመሆኑ በትጋት እንዲሰሩ እንደሚያበረታታቸው በመግለጽ በመንግስት ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review