ኢትዮጵያን የሚመጥናትን ስፍራ ለማስያዝ በአንድነት መስራት ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ኢትዮጵያን የሚመጥናትን ስፍራ ለማስያዝ በአንድነት መስራት ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እየተሰራች መሆኑን እና በዓለም መድረክ የሚመጥናትን ስፍራ ለማስያዝ ሁሉም ዜጋ በአንድነትና በጋራ መስራት እንደሚባው ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ‎”የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ነው፡፡

በዚህም በትምህርት ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በተመለከተም የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እያከናወኑት ያለውን ተግባር ያደነቁ ሲሆን ይህም ለሀገር እድገት በተቃራኒ የፖለቲካ ጎራ ያሉ ሰዎችም ጭምር በጋራ መቆም እንደሚችሉ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል እያከናወነች ያለችውን የጥረት ውጤት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በተለይም በበጋ ስንዴ ልማት የተገኘው ስኬት ሀገሪቱ በውጭ እርዳታ ላይ የነበራትን ጥገኝነት ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የተጀመረው ስራ የነዳጅ ወጪን ለመቀነስና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማምጣት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ያሉ ዘርፎች ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ መሰረት ለመጣል ታስበው እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል።

አሁን ያለው ትውልድ ለቀጣዩ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ራሱን መስዋዕት አድርጎ መስራት እንዳለበትም ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ህዝቡ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በበጀትም ሆነ በተለያዩ አማራጮች ምላሽ እንዲሰጡ አሳስበዋል ፡፡

“ኢትዮጵያ እየተገነባች ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሁሉም ዜጋ ለሀገር ልማትና አንድነት በጋራ እንዲቆም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በትዝታ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review