AMN – ሚያዝያ 25/2018 ዓ/ም
በአዲስ አበባ በተካሄደው ዛይድ የደግነት ሩጫ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች አትሌት ንብረት ኪዳኔ እና በሴቶች አለሽኝ ባወቀ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መስራች የሆኑትን የሼህ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያንን ሰብአዊ ራዕይ መነሻ በማድረግ የሚካሄደው ታዋቂው ዛይድ የደግነት ሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ተከናውኗል፡፡

መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ባደረገው ውድድር በወንዶች አትሌት ንብረት ክንዴ በቀዳሚነት ውድድሩን ያጠናቀቀ ሲሆን፤ አትሌት ኡርጌሳ ነጋሳ እና ግዛቸው ሙሴ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
ከሴቶች ደግሞ አትሌት አለሽኝ ባወቀ አንደኛ ደረጃ ፣ ሽቶ ጉሚ እና ሮቤ ዲዳ ተከታትለው በመግባት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።
የሻምበል ምሕረት