የሥራ ቡድኖች የአጀንዳ ምክረ-ሃሳቦቻቸውን ለሚያደራጀው ቡድን እያቀረቡ ነው

AMN- ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም

የሥራ ቡድኖች ሁሉም ቡድኖች ያዘጋጇቸውንና የተስማሙባቸውን ምክረ-ሃሳቦች እንዲያናብብ፣ እንዲያጣጥም እና እንዲያደራጅ ለተቋቋመው እና 120 አባላት ላሉት ቡድን እያቀረቡ ነው፡፡

ይህ ቡድን ከስምንቱ ባለ 500 አባላት የሥራ ቡድን በተመረጡ 15 አባላት የተዋቀረ ሲሆን መግባባት የተደረሰባቸውን የሁሉንም አጀንዳዎች ምክረሃሳቦች አዳምጦ የሚያጣጥም፣ በሚቀርቡ ሀሳቦች መካከል መጣረስ እንዳይኖር ጥንቃቄ የሚያደርግና ለጠቅላላ ሀሳቦቹ ወጥነት በመፍጠር 4 ሺ አባላት ላሉት ዋናው ጉባዔተኛ አደራጅቶ የሚያቀርብ ነው፡፡

ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት ከእያንዳንዱ የሥራ ቡድን የመጡ ምክረ-ሃሳቦችን በማዳመጥ ላይ መሆኑን ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review