በከንቲባ አዳነች አቤቤ ወደ አዘርባጃን ያመራዉ ልኡክ የካስፕያ ባህር ዳር የተቀናጀ የከተማ ልማት ፕሮጀክት ጎበኘ

You are currently viewing በከንቲባ አዳነች አቤቤ ወደ አዘርባጃን ያመራዉ ልኡክ የካስፕያ ባህር ዳር የተቀናጀ የከተማ ልማት ፕሮጀክት ጎበኘ

AMN- ግንቦት 12/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወደ አዘርባጃን ያመራዉ ልኡክ የካስፕያ ባህር ዳር የተቀናጀ የከተማ ልማት ፕሮጀክት (Sea Breeze Project) ጎበኘ፡፡

አዘርባጃኖች አሁን ባላቸው አድገናል ከተማ መልሶ ማልማትን አላቆሙም። ይልቁንም፥ አሮጌ መንደሮቻቸውን እያነሱ ያድሳሉ፣ እንደ “Sea Breeze ፕሮጀክት” ቀርፀው እስከአሁን ያልተጠቀሙባቸውን ቦታዎች ለይተው በ16 ዓመታት የሚጠናቀቁ 50 ሺህ ቤቶች ሆቴሎች እና ተያያዠ ልማቶችን እየገነቡ ነዉ። የግሉ ዘርፍ ከመንግስት ጋር በመቀናጀት በሰፊዉ እየሰሩ እንደሆነ አሳይተዋል።

በአዲስ አበባም፣ በየዓመቱ 100 ሺህ ቤቶችን እና ተያያዠ ልማቶችን ለመገንባት አቅደን በከፍተኛ ርብርብ እየሰራን እንገኛለን።

ያረጁ እና የተጎሳቀሉ አከባቢዎቻችንም ዕድሳት፤ ቀደም ብለን በአግባቡ ያልተጠቀምንባቸው አካባቢዎች እንደ የጫካ ፕሮጀክት፣ገላን-ጉራ፣ መሐመድያ መንደር፣ አዲስ ቱሞሮ ወዘተ. ያሉ አከባቢዎችን በመጠቀም አዲስ ከተማ የመገንባት ያክል ምቹ የልማትና የመኖርያ አካባቢዎችን የመፍጠር የመኖያ ቤት ችግርን የማቃለል እና የቱሪዝም መዳረሻ የመሆን ጉዟአችን አጠናክረን እየቀጠልን ነዉ።

የከንቲባ ጽ/ቤት ፤ በላቀ ጥረት፣ ቀጣይነት ባለው የልማት ልህቀት አዲስ አበባን እንደስሟ አበባ በማድረግ ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነቷን ግንባር-ቀደም እንድትሆን አበክረን እንሰራለን ብሏል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review