በደቡብ አፍሪካና በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን አግባብነት የሌለዉን ጥቃት ለማስቆም የተለያዩ ተግባራትና ወይይቶች እየተደረጉ ነዉ – የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

You are currently viewing በደቡብ አፍሪካና በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን አግባብነት የሌለዉን ጥቃት ለማስቆም የተለያዩ ተግባራትና ወይይቶች እየተደረጉ ነዉ – የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

AMN – ግንቦት 13/2018 ዓ.ም

በደቡብ አፍሪካና በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን አግባብነት የሌለዉን ጥቃት ለማስቆም የተለያዩ ተግባራትና ወይይቶች እየተደረጉ መሆናቸዉን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን ወዳጅነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለመ የሁለትዮሽ መዋቅራዊ ምክክር ስምምነት ባሳለፍነው ሳምንት በዋሽንግተን መፈራረማቸው አምባሳደር ነብያት ተናግረዋል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለወዳጅነት፣ ለትብብር፣ ለአጋርነት እና ለንግድና ለኢንቨስትመንት የምትሰጠውን ትኩረት የበለጠ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ከ120 በላይ ዓመታት ወዳጅነት ያላቸው ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የተፈራረሙት ስምምነት ሶሰት ዋና ዋና ነጥቦች ያሉት ሲሆን፣ የኢኮኖሚ በልፅግናና ንግድ እና ኢንቨስትመንት ፣ የመከላከያና የፀጥታ ትብብርን ማጠናከር እንዲሁም ቀጠናዊ ሰላምና ደህንነትን ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን አምባሳደር ነብያት ገልፀዋል።

የተባበሩት መንግስታት 80ኛ ዓመቱን እያከበረ መሆኑን ምክንያት በማድረግ ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲን የበለጠ የሚያጠናክሩ ተግባራትን ኢትዮጵያ ማከናወኗንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራች ሀገር እንደመሆኗ፣ በ80 ዓመታት የድርጅቱ ጉዞ ውስጥ የተለያዮ ሀገራትን ሰላም ከማስከበር ጀምሮ ለቀጠናው ደህንነት ኢትዮጵያ የማይተካ ሚና መጫወቷን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

በዚህም “በሰላም አብሮ ለመኖር” በሚል 4 ቴምብሮች አሳትማ ማበርከቷን አስታውሰዋል።

ሌላው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የኢትዮጵያ ጉብኝትን ተከትሎ በተደረጉ ውይይቶች በታዳሽ ሀይል፣ በተቀናጀ የሀይል አቅርቦትና መሰል ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱን አምባሳደር ነበያት ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በተሳተፈችበት የብሪክስ ስብሰባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በተለይም ከህንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት የበለጠ በሚያጠናክሩ ዘርፎች ላይ መክረወዋል ብለዋል።

ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በተመለከተ በደቡብ አፍሪካና በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ያለአግባብ ጥቃት ለማስቆም የተለያዩ ተግባራትና ወይይቶች መደረጋቸውንም ተናግረዋል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review