የኮሙኒኬሽን እና የሚድያ አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ የኪነ ጥበብ፤ የስፓርትና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች አረንጓዴ አሻራቸዉን አኖሩ

AMN ሐምሌ 7/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ጨምሮ የመንግስት እና የግል ሚድያ አመራሮች፣ ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የኮሙኒኬሽን መዋቅር የኪነጥበቡ ቤተሰብ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የስፖርት ቤተሰብ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የማህበረሰብ አንቂዎች በጋራ በመሆን በየካ ክፍለ ከተማ ቀበና ወንዝ ዳርቻ ላይ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሔደዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚኣብሄር “የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ተቋማት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ ባሉ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች የጀርባ አጥንት በመሆን በመንግስትና በህዝብ መካከል ድልድይ ሆኖ ከማገልገል በተጨማሪ፣ አሰባሳቢ የወል ትርክትን በማስረፅ፣ የሀገር አንድነት እና ሉአላዊነትን የጠራ ዕሳቤ ያለው ትውልድ ከመፍጠር አንፃር ትርጉም ያለው ስራ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

እነዚህ ተቋማት ስለ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስፈላጊነት ተከታታይ ዘገባዎችን ከመስራታቸዉ በተጨማሪ በመርሃ ግብሩ ላይ በመሳተፍ ግንባር ቀደም ሚናቸዉን በመወጣት ላይ መሆናቸዉን አስገንዝበዋል፡፡

የሚድያዉ ቤተሰብ በከተማዋ ሁለንተናዊ አጀንዳዎች ላይ ግንባር ቀደም ሆነው በትዉልድ እና በሃገር ግንባታ ላይ ሙያዊ ግዴታቸዉን ለመወጣት ድርብ ኃላፊነት ያለባቸዉ መሆኑን በመጥቀስ ይህንንም ወደ ተግባር ለዉጦ የተፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት የጀመሩትን ስራዎች አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ መግለጻቸዉን የቢሮዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስተባባሪነት መካሄዱም ተገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review