AMN – ግንቦት 14/2018 ዓ.ም
የዲሞክራሲ ልምምድን የመቅረጽ፣ የመግራት፣ የማስፋት እና የማጽናት ሚና ተቀዳሚ የሚዲያ ተቋማት የቤት ሥራ መሆኑ ተመላከተ።
መጪውን 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ሀገርን በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባበት እና በመደመር ምን ያህል ታላቅ ነገር ማሳካት እንደሚቻል ለዓለም በተግባር ማሳየት የሚቻልበት የታሪክ አጋጣሚ ማድረግ እንደሚገባም ተገልጿል።
ጀግኖች አባቶች ከአድዋ ዜሮ ዜሮ ተነስተው፣ በአንድነት ጸንተው ነጻ ሀገር እንዳስረከቡን ሁሉ፤ የሚዲያው ዘርፍም ለኢትዮጵያ ከፍታ በቃል ኪዳን ታስሮ ስለሀገር እድገት በአንድነት ተነስቷል።

የዲሞክራሲ ግንባታ የሀገረ መንግሥት ማጽኛ ከሆኑት ዋና ዋና ምሶሶዎች አንዱ መሆኑ በተመከረበት በዚህ መድረክ፤ የዲሞክራሲ ልምምድን የመቅረጽ፣ የመግራት፣ የማስፋት እና የማጽናት ሚና የሁሉም ሚዲያዎች ቀዳሚ የቤት ሥራ መሆኑ በተሣታፊዎች ተሰምሮበታል።
ከ25 በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ የሚዲያ ተቋማት በተሳተፉበት በዚህ የውይይት መድረክ፤ ሚዲያዎች በሀገር ብሔራዊ ጥቅም ላይ እንዴት በትብብር መሥራት እንዳለባቸው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በዚህም መሠረት 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በስኬት ለማጠናቀቅ የዕውቀት፣ የግብአት እና የሰው ኃይልን በማቀናጀት በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የጋራ ውል ታስሯል፡፡ መረጃው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው።