አዲስ አበባ በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ በሚገኘዉ የአለም የከተሞች ፎረም ላይ ተሞክሮዋን አቀረበች

You are currently viewing አዲስ አበባ በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ በሚገኘዉ የአለም የከተሞች ፎረም ላይ ተሞክሮዋን አቀረበች

AMN – ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ በሚገኘው 13ኛው የአለም ከተሞች ፎረም ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፎርሜሽን እና የመሰረተ ልማት ፋይናንሲንግ ተሞክሮዎች ቀርበዋል።

አምስተኛ ቀኑን በያዘሙ ፎረም “የከተሞች ድምፅ” በተሰኘው መድረክ እና በ UN HABITAT Arena በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ የከተማዋ የልማት ጉዞ በስፋት ተዳስሷል።

በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ አዲስ አበባ በቅርብ አመታት ያስመዘገበቻቸው የትራንስፎርሜሽን ስራዎች ሰው ተኮር እና በራስ አቅም የተከናወኑ ተሻጋሪ ፕሮጀክቶች መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ስራዎቹ ብቁ የፕሮጀክት አስተዳደር፣ የተሳካ ትግበራ እና ከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነት የታየባቸው መሆናቸው በሰፊው ተብራርቷል።

እነዚህ የአዲስ አበባ ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ እና በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ከተሞች ጠቃሚ ልምዶችን የሚያካፍሉና ትልቅ ትምህርት የሚወሰድባቸው መሆናቸውም በመድረኩ ላይ መመላከቱ ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review