በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነባውን የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነባውን የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ግንቦት 16/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ትላንት ምሽት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ 18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነባውን የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ብለዋል።

ፓርኮቹ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን እንዲሁም ድልድዮችን፣ የተለያዩ 6 ስፖርት ማዘውተሪያዎችን ፣ 7 የህጻናት መጫዎቻዎችን ፣አረንጓዴ ስፍራና የአትክልት አጸዶችን፣ 6 ካፍቴሪያዎች፣ 3 አንፊ ትያትሮችን እና ልዩ ልዩ መናፈሻዎችን እንዲሁም በርካታ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶችን ያካተቱ ናቸው።

ይህም በሁሉም ደረጃ የሚካሄዱ የልማት ስራዎቻችን አካታች እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እንደፍላጎቱ የሚጠቀምባቸው እንዲሆኑ የያዝነው አቅጣጫ ማሳያ ነው ብለዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች በጋራ ላሳዩት ድንቅ ስራ በጣም እናመሰግናለን ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review