አዲስ አበባ ውብ ከተማ ናት – የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ኢማኑኤል ኤቡኤ

You are currently viewing አዲስ አበባ ውብ ከተማ ናት – የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ኢማኑኤል ኤቡኤ

AMN – ግንቦት 30/2018 ዓ.ም

የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ኢማኑኤል ኤቡኤ በአዲስ አበባ ውበት መደነቁን ገለፀ።

አዲስ አበባ ውብ ናት ያለው ኢማኑኤል ኤቡኤ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገለትም ተናግሯል።

አርሰናል የ2026 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ በአዲስ አበባ በተካሄደው የደስታ መግለጫ ዝግጅት ተካፋይ ለመሆን ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ኢማኑኤል ኤቡኤ እና የኤ ኤፍ ቲቪ (የአርሰናል ደጋፊዎች ቴሌቪዥን) አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

እንግዶቹ አዲስ ስፖርት ፓርክን ጨምሮ የተለያዩ የከተማዋን የልማት ስራዎች የጎበኙ ሲሆን በከተማዋ ልማት መደነቃቸውን ገልጸዋል።

ኢማኑኤል ኤቡኤ በአዲስ አበባ በተመለከተው ዘመናዊነት መደነቁን ተናግሯል።

ናናቲ የተሰኘችው ጎብኚ በበኩሏ የከተማዋ አረንጓዴነት፣ ጽዳት እና አጠቃላይ ውበት እጅጉን ማራኪ ሆኖ እንዳገኘችው ገልጻለች።

ትውልደ ጃማይካዊ የአርሰናል ደጋፊ፤ የአዲስ አበባ ምቹ የአየር ንብረት፣ የነዋሪዎቿ እንግዳ ተቀባይነት እንዲሁም የከተማዋ ዘመናዊነትና ፈጣን እድገት እንደተደነቀ ተናግሯል። በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውም ነው የገለፀው።

የከተማዋን ፈጣን ልማት ስራዎች፣ የአረንጓዴ መናፈሻዎች መስፋፋት እና የነዋሪው እንግዳ ተቀባይነት አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የቱሪዝም ተመራጭነት ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን ጎብኚዎቹ አመላክተዋል፡፡

በትዝታ መንግሥቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review