AMN- ሰኔ 05/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚጀመርበትን ዕለት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ስጥቷል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርያ (ፕ/ር) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የምክክር ጉባኤው ሀምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ገልፀዋል::
በ12 ክልልሎች ሰፊና ጥልቅ የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ መከናወኑን የገለፁት መስፍን አርያ (ፕ/ር)፣ በወረዳ ደረጃም 93 በመቶ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል::
ይህ ታሪካዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የሚከናወን መሆኑን ያነሱት ዋና ከሚሽነሩ፣ በጉባኤው 4 ሺህ የሚሆኑ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የህዝብ ተወካዮች እንደሚሳተፉ በመግለጽ፣ ሀገራዊ መግባባትን ያመጣሉ በተባሉ ወሳኝ አጀንዳዎች ላይ ይመከራል ብለዋል።
በራሄል አበበ