ዳግም ንግስናውን ያስመሰከረው ሊዮኔል ሜሲ

AMN ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

እግሮቹ የ38 አመት እድሜን የቆጠሩ አይመስሉም ፤ ዛሬም እንደ 18 ዓመት ተጫዋች በጥልቀት ይከላከላሉ በፍጥነትም ያጠቃሉ።

ብዙ ታላላቅ ተጫዋቾች በእርሱ እድሜ ሲደርሱ እግሮቻቸውን ማዘዝ ተስኗቸው እግር ኳስን እስከወዲያኛው ተሰናብተው ጫማቸውን ሰቅለዋል። እርሱ ግን ዛሬም በሜዳው መሀል ታላቅ ስራን እየሰራ ይገኛል። ሰውነቱ ላይ ምንም አይነት የድካምና ጫናን አይታይም በየትኛውም የሜዳው ሳር ላይ እንደፈለገ ሲንቀሳቀስ ታይቷል።

ይህ ሰው በእግር ኳስ ያላሳካው አንዳችም ክብር የለም ይሁን እንጂ ዛሬም ድረስ የድል ርሀቡ አብሮት አለ። ለሊት አርጀንቲና ከአልጄሪያ ጋር በነበራት ጨዋታ ላይ 17ኛው ደቂቃ ላይ ሊዮኔል ሜሴ አርጀንቲናን ቀዳሚ ያደረገች ጎብ ሲያስቆጥር የተደሰበት መንገድ 8 ጊዜ ባላንዶር ያገኘ ከሀገሩ ጋርም የዓለም ዋንጫን ያነሳ አይመስልም። ደስታውን የገለፀበት መንገድ በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያውን ጎብ ያገባ ይመስል ነበር።

በዚህ ሰው ፊት እድሜ ተራ ቁጥር ብቻ ነው ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ እያደር እንደወይን መጣፈጡን ተክኖበታል። በዘመኑም ከዘመኑም በፊት ያሉ ክብሮወሰኖችን ሁሉ በእጁ አድርጓል። እግርኳስ ሊዮን በተለየ መልኩ ልታከብር ይገባታል ይህ ሰው የእግርኳስ አለም ንጉሰ ነገስት ነው።

አርጀንቲና እድለኛ ናት ፤ ብቻውን ድንቅ የሚያደርግ ከምንም ነገር ተነስቶ ተዓምር መስራት የሚችል ሜዳ ውስጥ ከሚሰለፉ 22 ተጫዋቾች የሚልቅ ንጉሰ ነገስት ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ የሚባል ጥበበኛ ተሰጥቷታል።

ሜሲ ትናትና ምሽት 200ኛ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ አድርጓል በእነዚህ ጨዋታዎች ደግሞ ለሀገሩ 119ኛ ጎቦቹን አስቆጥሯል። ሀትሪክ መስራት መቻሉ ደግሞ በአለም ዋንጫ ውድድር 16 ጎቦችን በማስቆጠር ለአመታት በጀርመናዊው ሚሎስላቭ ክሎስ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን መጋራት ችሏል።

አሁን ሊዮ ከዚህ በኃላ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚያስቆጥራቸው ጎቦች ክብረወሰኑንን ለብቻው እንዲይዘው ያደርጋል።

ሊዮ በስንት ጎሎች ክብረወሰንን ለብቻው ማድረግ የሚችል የመስላቹሃል? ሀሳባችውን በኮሜንት አሳውቁን

በብንያም ከድር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review