ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት የ75 የምርጫ ክልሎችን ውጤት አፀደቀ

AMN- ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ ቆጠራ እና የማዳመር ሥራ የተጠናቀቀባቸው የ75 የምርጫ ክልሎችን ውጤት አፅድቆ ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ አጠቃላይ የምርጫ ውጤት የማረጋገጥና ኦዲት የማድረግ ሥራን፣ የቀረቡ ቅሬታዎችን እና የተሰጡ ውሳኔዎች በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚሁ መሠረት በየምርጫ ክልሎቹ የተመዘገቡ የ35 የክልል ምክር ቤት እና የ40 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውጤቶች በቦርዱ በዝርዝር ተብራርተዋል።

ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ያጸደቃቸውን የ75 የምርጫ ክልሎች ውጤት ጨምሮ የ723 የምርጫ ክልል ውጤቶችን አፅድቋል፡፡

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review