ከ28 ዓመት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ የተመለሰችው ኖርዌይ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች

You are currently viewing ከ28 ዓመት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ የተመለሰችው ኖርዌይ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች

AMN-ሰኔ 16/2018 ዓ.ም

ኖርዌይ ሴኔጋልን በማሸነፍ የጥሎ ማለፍ ዙር መቀላቀሏን አረጋግጣለች።

በኒውዮርክ ኒውጀርሲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኖርዌይ 3ለ2 ስታሸንፍ ኧርሊንግ ሀላንድ የሁለቱ ግቦች ባለቤት ሆኗል።

የ25 ዓመቱ የማንችስተር ሲቲ አጥቂ በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫው ያስቆጠራቸውን ግቦች አራት አድርሷል። በአጠቃላይ ለሀገሩ ካደረጋቸው 52 ጨዋታዎች 59 ግብ በስሙ አስመዝግቧል።

ማርከስ ፔደርሰን ሌላኛውን የኖርዌይ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ኢስማኤላ ሳር ልዩነት ያልፈጠሩ የሴኔጋል ግቦችን አስገኝቷል።

ከ28 ዓመት በኋላ ወደ ታላቁ መድረክ የተመለሰችው ኖርዌይ በምድብ ዘጠኝ ከፈረንሳይ እኩል ስድስት ነጥብ በመያዝ ወደ ጥሎ ማለፉ አልፋለች። ሁለቱ ሀገራት በቀጣይ የምድቡ የበላይ ለመሆን እርስ በእርስ ይጫወታሉ።

የተሻለ ርቀት ትጓዛለች ተብላ የተገመተችው ሴኔጋል በውድድሩ ያላት ቆይታ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በቀጣይ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋ ኢራቅን ትገጥማለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review