የመኖሪያ ቤት ኪራይ ገበያን ሚዛናዊ ለማድረግ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው – የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ

You are currently viewing የመኖሪያ ቤት ኪራይ ገበያን ሚዛናዊ ለማድረግ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው – የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ

AMN – ሰኔ 19/2018 ዓ.ም

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ገበያን ሚዛናዊ ለማድረግ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም የወጣውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ መሰረት በማድረግ በተካሄደ ጥናት ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚህ ውይይት ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ፣ መንግሥት የሕግ የበላይነትንና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው ብለዋል።

በዚሁ መሠረትም የቤት ኪራይ መረጃ በመመዝገብና የኪራይ ዋጋ ማስተካከያ ላይ ጥናት በማካሄድ ሚዛናዊ የኪራይ ዋጋ እንዲኖር እየተሠራ ነው ብለዋል።

በመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ የተካሄደው ጥናት የአዲስ አበባን ተጨባጭ ሁኔታ ያማከለ ሲሆን፣ በቤት ባለቤቶችና በተከራዮች መካከል የመተማመን ስሜት እንዲፈጠርም ያግዛል ብለዋል።

በተጨማሪም ጥናቱ የከተማዋን ነዋሪዎች የመክፈል አቅም መሠረት ያደረገ በመሆኑ የኢኮኖሚና የንግድ እንቅስቃሴንም ያረጋጋል ብለዋል።

በባለሙያዎች በተካሄደው በዚህ ጥናት ላይ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፣ የቤት ባለቤቶች እና ተከራዮችን የሚወክሉ የማኅበረሰብ ተወካዮች እየተወያዩበት ይገኛሉ።

በጌታሁን ከተማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review