በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የስርዓተ ጾታ ኦዲት ሊደረግ ነው

You are currently viewing በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የስርዓተ ጾታ ኦዲት ሊደረግ ነው

AMN- ሰኔ 23/2018 ዓ.ም

በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የስርዓተ ጾታ ኦዲት ጥናት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ለተውጣጡ ሴት ባለሙያዎች ስርዓተ ጾታ በመገናኛ ብዙሃን አካታችነትን በተመለከተ የስልጠና መርሐ ግብር እያካሄደ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ፣ በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሴት ባለሙያዎች ባላቸው የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ ከወንዶች አቻዎቻቸው እኩል እድል ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡

በዘርፉ የሚስተዋለውን ሴቶችን ጠንከር ባሉ ጉዳዮች ላይ አለማሰማራት ችግርን ለመፍታት የሚያስችሉ አሰራሮች ለመዘርጋት የኦዲት ፖሊሲው ጠቀሜታው የጎላ ስለመሆኑም ዳይሬክተሯ አብራርተዋል፡፡

ለዚህ የሚረዳ የስርዓተ ጾታ ኦዲት በሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ በቀጣይ ሶስት ወራት ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ከሁሉም የመገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ ባለሙያዎች የዘርፉ ምሁራንና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በዝናሽ ሞዲ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review