AMN— ሰኔ 25/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ በቦሌ ክፍለ ከተማ ኤርፖርት ቪአይፒ መግቢያ አካባቢ የአረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡
በመርሐ ግበሩ ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ኢንጅነር አያልነሽ ሐብተማርያም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሀገርን ቀጣይነት የሚወስን ትልቅ ስራ ነው ብለዋል፡፡

ቢሮው በሚያከናውናቸው ተግባራት እና በሚገነባቸው የአገልገሎት መስጫ ተቋማት ላይ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን የመገንባት የሁል ጊዜ ስራው እንደሆነም አክለዋል።
የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ እና ለፅድቀት የማብቃት ባህል ሊለመድ እንደሚገባም ኢንጅነር አያልነሽ ሐብተማርያም አጽኖት ሰተዋል፡፡

በችግኝ ተከላው የተሳተፉ የቢሮው ሰራተኞችም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለትውልድ የሚሻገር ተግባር በመሆኑ እኛም መሣተፋችን ደስተኛ አድርጎናል ብለዋል።
ሰራተኞቹ አክለውም የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ለፅድቀት ማብቃት ከእኛ የሚጠበቅ ተግበር ነው ብለዋል።
በመሀመድኑር ዓሊ