አገልጋይና ዋርካ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች አገልግሎትን ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ አግዘዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing አገልጋይና ዋርካ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች አገልግሎትን ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ አግዘዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ሐምሌ 05 /2018 ዓ.ም

በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሚሰራጩት አገልጋይና ዋርካ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በመዲናዋ አገልግሎቶች ግልጽና ተጠያቂነትን ያሰፈኑ እንዲሆኑ እገዛ ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ ይህን የገለጹት ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ነው፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ አገልግሎትን ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሚተላለፉ “ አገልጋዩ ” የሚል አመራሩ ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበት የቀጥታ ስርጭት እና “ ዋርካ ” የተሰኙ ፕሮግራሞች አገልጋዩና ሕዝቡ በአካል ተገናኝቶ ፊት ለፊት የሚጠያየቅበት ኘሮግራም መተግበሩን ገልፀዋል ፡፡

በፕሮግራሞቹ ከተነሱ የተገልጋይ ጥያቄዎች መካከል 89 % የሚሆኑት ችግሮች መፈታታቸውን ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ይህ አሰራር በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሥር ሰዶ የቆየውን ዳተኝነት በመቅረፍ ረገድ ጠንካራ የተጠያቂነት ሥርዓት የጣለ ሲሆን፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክፍተትና ግድፈት በፈጠሩ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ላይ አስተማሪና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማስቻሉን ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡

በትዝታ መንግሥቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review