AMN ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም
የኢፌድሪ መሶብ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመሶብ አገልግሎት የሚመራበት የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ አስመለክቶ ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች ከመጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
የመሶብ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ አለማየሁ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ከሙስናና ብልሹ አሰራር የፀዳ ፈጣንና ቀልጣፍ የአገልግሎት ስርአትን ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ስትራቴጂክ እቅዱ በዋናነት ከዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 የተቀዳ አገልግሎትን የማዘመን ፤ ጊዜና ወጪን የመቀነስ ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ማዕከላቱን በሁሉም ክልሎችና ከተሞች ተደራሽ ማድረግ ላይ ያተኮረ ነው ያሉት ዋና ስራ አሰፈፃሚው ውይይቱ ግብአት የሚገኝበት ነው ብለዋል።

ከተሞችና ክልሎች የዲጂታል ማዕከላቱን አሰራር በብቃት እንዲተገብሩ ድጋፍ ማድረግ ፤ ግልጽነት የተሞላበትና በውጤት ላይ የተመሰረተ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት መዘርጋት አስመለክቶ ሠፊ ማብራሪ በስትራቴጅክ እቅዱ ቀርቧል ።
በሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም በአንድ የመሶብ አገልግሎት መስጫ ተቋም የጀመረው አገልግሎቱን የማዘመን ተግባር አሁን ላይ ወደ 100 የመሶብ ማዕከላት አና ወደ 3 ተንቀሳቃሽ ከፍ ማለቱም በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በራሄል አበበ