AMN ሐምሌ 27/2018
በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በይፋ ተጀምሯል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ መርሐ ግብሩን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የ2018 የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በመላው ኢትዮጵያ መጀመሩን አብስረዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው መሳተፍ መጀመራቸውን ያነሱት ሚንስትሯ አዲስ አበባ ከሚገኘው ከሁኔታ መከታተያ እና የመረጃ ማደራጃ ማዕከል መረጃዎች በተከታታይ ይፋ እንደሚደረጉ አስታውቀዋል።
ለዘንድሮው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 853 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል።
በካሳሁን አንዱዓለም