AMN ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

በዶሃ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች፣ ሠራተኞች እና በቀጠር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በሚሲዮኑ ቅጥረ-ግቢ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተካሂዷል። ።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ በቀጠር በኢራንና በየመን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፈይሰል አሊይ አብራሂም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ በቅርቡ የምታስተናግደውን የኮፕ 32 (COP32) ጉባኤ የሚያስተዋውቅ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አርአያና መሪ መሆን የምትችል ታላቅ ሀገር መሆኗን አስመስክራለች ብለዋል።

በዶሃ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ በመሳተፋቸዉም ምስጋና አቅርበዋል፡፡