AMN- ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም
የማህበራዊ ክላስተር የ12 ወራት አፈፃፈም ሪፖርት ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የክረምት በጎ ፍቃድ ሥራዎች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መክሯል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊና የቅንጅታዊ ስራዎች የማህበራዊ ልማት ክላስተር አስተባባሪ ተወካይ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ በክላስተሩ ስር የሚገኙ ተቋማት በ2018 የበጀት ዓመት እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል፡፡
በቀጣይም በክላስተሩ የሚገኙ ተቋማት በተዘጋጀው እቅድ መሰረት የተሻለ ስራ ለመስራት ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው አመላክተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የተቋማት ክትትል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞላ ንጉስ ፣ ክላስተሩ በ2018 የበጀት ዓመት የታዩ ውጤታማ ተግባራትን በማስቀጠልና የተስተዋሉ ክፍተቶችን በመለየት በ2019 የበጀት ዓመት የተሻለ ውጤትን ማስመዝገብ ይጠበቅበታል ብለዋል።

የክላስተሩ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በየሩብ ዓመቱ በተቋማት በመገኘት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ የድጋፍና ክትትል ስራ ሲሰሩ መቆየታቸውን የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ እና የዘርፉ አስተባባሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ናቸው፡፡
በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡና በክላስተሩ ስር ለተደራጁ ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።
በተመስገን ይመር