AMN- ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናልን መርቀው ከፍተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ባሕር ዳር ታሪክ ከተፈጥሮ ሁለቱም ሳይሰስቱ ውበት ያበዙላት ታሪክ ያጠገቧት ለኢትዮጵያውያን ከዕኛም አልፎ ለአፍሪካውያን የልማት የብልጽግና፣ የለውጥ፣ የዕድገት ምሳሌ መሆን የምትችል ከተማ ነች ብለዋል፡፡
አዲሱ ተርሚናል በግዙፍነቱ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቀጥሎ ሁለተኛው መሆኑንም ገልጸዋል።
ባሕር ዳር ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቱሪዝም፣ በኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ፣ በውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ በግዙፉ የዓባይ ድልድይ እና በኮሪደር ልማት ከፍተኛ መነቃቃት ውስጥ እንደምትገኝ አንስተዋል፡፡