
የአጠናቃሪ ቡድኑ ሥራ : – ከስምንቱ ቡድኖች የተወጣጡ 120 አጠናቃሪዎች ሁሉንም የአጀንዳና የምክር ሀሳቦች በጥንቃቄ አዘጋጅተው አንድ ወጥ ሰነድ አጠናቀዋል።
የግብአት መሰብሰብ ሂደት :- ዛሬ እያንዳንዱ ቡድን የሌሎችን የምክር ሀሳቦች በመስማትና በመገምገም ተጨማሪ አስተያየቶችና ግብአቶችን ሲሰጥ ውሏል።
የሰነድ ማጠናቀቅ :- አጠናቃሪ ቡድኑ የተሰጡትን የመጨረሻ ግብአቶች አካትቶ ዛሬ ምሽት ሰነዱን ሙሉ በሙሉ ያጠናቅቃል።
ቀጣይ እርምጃ :- ነገ የተጠናቀቀው የመጨረሻ ሰነድ ለ4ሺህ የምክክር ጉባኤው ተሳታፊዎች ይቀርባል።
ለህዝብ የተላለፈ መልእክት :- ህብረተሰቡ በተዛቡ መረጃዎች ሳይወዛገብ ትክክለኛ የሆኑ ሚዲያዎችንና የኮሚሽኑን ይፋዊ መግለጫዎች ብቻ እንዲከታተል ጥሪ ቀርቧል።