የኢትዮጵያውያን የትብብር ማሳያ – አረንጓዴ ዐሻራ

AMN – ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር የተፈጥሮ ሀብቶችን በመጠበቅ የአካባቢን ስነ-ምህዳር አሻሽሏል፡፡

ትውልዱ እንደ ሀገር እየተከናወነ ባለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ – ግብር በመሳተፍ የተራቆቱ አካባቢዎችን አረንጓዴ በማልበስ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል፡፡

ባለፉት 8 ዓመታት ኢትዮጵያውያን አዲስ ታሪክን የፃፉ ሲሆን ይሄም ለተተኪው ትውልድ አረንጓዴ የለበሰች ሀገር ለማስረከብ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡

ዜጎች በጋራ ችግኞችን በመትከል ለቀጣዩ ትውልድ የመተባበርን እንዲሁም በጋራ ለውጥ የማምጣትን ሂደትንም እያስተማሩበት ይገኛል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ – ግብር በሀገር አቀፍም ሆነ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ምህዳራዊ ውጤቶችን አስመዝግቧል። ይሄም የኢትዮጵያውያን የትብብር ውጤት ነው፡፡

እንደ ሀገር የነበረው የደን ሽፋን ማደግ፣ ለጎርፍ አደጋ እንዲሁም ለአፈር መሸርሸር ተጋልጦ የነበረውን መሬት መልሶ ማገገም እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የመርኃ – ግብሩ ውጤቶች ናቸው፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ – ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማም ተግባራዊ እየሆነ ካለው የኮሪደር ልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር ተቀናጅቶ በመሰራቱ የከተማዋን ውበትና ጽዳት ከፍ አድርጓል፡፡

ኢትዮጵያን እና አዲስ አበባን ውብ ከማድረግ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ፣ የስነ-ምህዳር ሚዛንን የሚጠብቅ እንዲሁም ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ ሀገራዊ ስኬት ሆኖ እየቀጠለ ነው፡፡

በሌላ በኩል ለሥራ እድል ፈጠራም ጉልህ ሚና እየተጫወተ ሲሆን ከችግኝ ማፍላት ጀምሮ እስከ እንክብካቤ ድረስ ለበርካታ ዜጎች በተለይም ለወጣቶች እና ለሴቶች የገቢ ምንጭ እየሆነ ነው፡፡

ህብረተሰቡም በጋራ በመሥራት ጠንካራ የሥራ ባህል እንዲያዳብር አድርጓል።

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review