በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ2 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ2 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

‎AMN- ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 494 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

‎‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 12 ዙር በረራ የተመለሱት 2 ሺህ 312 ወንዶች፣ 163 ሴት እና 19 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ፣ ከተመላሾች መካከል189 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።‎

‎መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስከ አሁን ከ96 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

‎‎ሚኒስቴሩ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን፣ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review