76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

AMN- ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም

76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ በአዲስ አበባ በአድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል።

በመርሃ ግብሩ የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር መሀመድ ያኩብ ተገኝተዋል።

እንዲሁም ከ47ቱ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ አባል ሀገራት የተውጣጡ የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የልማት አጋሮች በተጨማሪም የቀጣናውና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች ታድመዋል።

ጉባኤው በአፍሪካ ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ስርዓት መገንባት፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ፣ ዲጂታል የጤና ስርዓት መገንባት፣ የጤና ባለሙያዎች አቅም ግንባታና የሀገር ውስጥ ምርቶችን ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይም ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተመስገን ይመር

See less

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review