የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በመጠፋፋት እና መገፋፋት ብሎም የሴራ ትንተና ላይ የተመሰረተዉን የኢትዮጵያን የፖለቲካ አዉድ የቀየረ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መሆኑን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተነገሩ፡፡
ይህ አዲስ የሀገር እሳቤ እና ጉዞ የኢትዮጵን ፖለቲካ ከጠመንጃ አፈሙዝ እና ከሀይል አመራጭ አላቆ ለሀገር ሰላምን በሚያሰፍን እና በመነጋገር ዉስጥ መስማማት እንዳለም ፍንጭ የሰጠ ሆኗል ብለዋል፡፡
ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ሀገራዊ ምክክሩ በመገፋፋት እና በመጠፋፋት ብሎም በሴራ ትንተና ላይ ለተመሰረተዉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ አዉድም አዲስ ምዕራፍን የከፈተ ነዉ ብለዋል፡፡
የህዳሴ ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ሱራፌል እሸቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ህዝብን ያቀራረበ ማህበራዊ መስተጋብርንም በዉልም የገለጠ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ነዉ ብለዋል፡፡
ምክክሩ በተለያዩ የፖሊቲካ ርዕየተ አለም እና እሳቤ ለተለያዩ መርሆችም የሚገዙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዊችን በማሰባስብ ሀገርን ያስቀደመ እና ህዝብን ማዕከል ያደረገ ንግግር ያረጉ ዘንድ እድልን ፈጥሯልም ብለዋል፡፡
የወሎ ህዝቦች ድሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ነጻነት ጣሰዉ ምክክሩ የኢትዮጵን የፖለቲካ ምህዳር መስፋት ለኢትዮጵያም አዋጭ መንገድን መቀየስ እና ከችግር መዉጫ አመላካች ሃሳቦችን ማመንጨት የተቻለበት ነዉ ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት ሊቀመንበር አቶ ገብሩ በርሄ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገርን መልክ ተላብሶ በልዩነት ዉስጥ አንድነትን አክብሮ አካታችነቱንም በዉል አረጋግጦ ስለመደረጉም ተናግረዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ ከጠመንጃ ባለፈ ንግግርን ያስቀደመ ከስሜት በተሻገረ ምክንያታዊነትን ያስቀደመ ትዉልድን ለመፍጠር እና በቀጣይ ጠንካራ ሀገርን እዉን ለማድረግ ዛሬ ላይ መሰረት ተጥሏል ያሉት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ይህ ለዛሬዉ ትዉልድ ትልቅ የድል አሻራ ለነገ ትዉልድ ደግሞ ታሪካዊ ቅርስ መሆኑንም የፓርቲዎቹ የስራ ሃለፊዎች ተናገረዋል፡፡
በተመስገን ይመር
ይህን ዜና ይዘቱ ሳይቀነስ እና ሳይጨመር የታሪክ ፍሰቱን፣ የቃላት አጠቃቀሙን እና የፊደል ግድፈቱን በማረም አዘጋጅልኝ