AMN – መስከረም 13/2019 ዓ.ም
አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር እንደ መሆኗ መጠን፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከተማ መዋቅር፣ በማህበራዊ አገልግሎቶች እና በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ረገድ ከፍተኛ እና ተከታታይ ለውጦችን እያስመዘገበች ትገኛለች።
የከተማ አስተዳደሩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና የከተማዋን ከፍታ ከዘመኑ ጋር ለማጣጣም የኮሪደር ልማት እና የከተማ ገጽታ ማሻሻያ አድርጓል፡፡
ማህበራዊ ጥበቃ እና የህዝብ አገልግሎቶችን፣ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የኑሮ ውድነትን በመቆጣጠር እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን አሰራሮችን በመዘርጋት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ ይገኛል፡፡
መስተዳደሩ ከተማዋን ጽዱ፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ ሰፊ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን አከናውኗል።
ይህም ሰፋፊና ምቹ የእግረኛ መንገዶች፣ አዳዲስ አደባባዮች እና አረንጓዴ ቦታዎች መገንባታቸው የከተማዋን ገጽታ በእጅጉ ለውጠውታል።
የከተማውን የፍሳሽ መስመሮች እና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድን ማዘመን ለአካባቢ ጤናማነት እና ለከተማው ነዋሪዎች ንጹህ አየር መፈጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል።
የከተማው አስተዳደሩ ዜጎችን ማዕከል ያደረጉ ማህበራዊ ጥበቃ እና አቅርቦት ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል።
በዚህም የጤና አገልግሎት ተደራሽነን ለማረጋገጥ አዳዲስ ሆስፒታሎች፣ የጤና ማዕከላት እና ክሊኒኮች ግንባታ በመስፋፋቱ እና በዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች በመደራጀታቸው የህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

በትምህርት ዘርፍ ልማት፡ አዳዲስ የትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ ነባሮችን የማደስ እና በትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት ላይ የተደረጉ ስራዎች ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ አካባቢን በመፍጠር የትምህርቱን ጥራት ለማሻሻል አስችለዋል። በተጨማሪም ለወጣቶች የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች ትኩረት ተሰጥቷል።
የኑሮውን ውድነት ለመቆጣጠር እና የግብይት ስርዓቱን ለማስተካከል የተገነቡ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት እና የሸማቾች ማህበራት ሚና ከፍተኛ ነው።
በዚህም በኮንስትራክሽን፣ በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች ለብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ ዘርፎች የስራ እድል ተፈጥሯል።
ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንጻር በከተማው የሚከናወኑ ሁለገብ ስራዎች በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ አድርገዋል።
በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን አሰራር በማስፋፈፋት፤ የሰነዶች ማረጋገጫ፣ የንግድ ፈቃድ እና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማቅረብ መጀመሩ የአስተዳደሩን ቅልጣፌ አሳድጎታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶች የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ማህበራዊ ደህንነት ከፍ የሚያደርጉ ናቸው።
እነዚህ ሁለገብ ልማቶች አዲስ አበባን ከቀን ወደ ቀን ተወዳዳሪ እና ለኑሮ ምቹ ከተማ ከማድረግ አልፎ ለአገራዊ ኢኮኖሚ እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ እጅግ የላቀ ነው።
በፍሬሕይወት ብርሃኑ