መስቀል በአብሮነት፤ በመተሳሰብ እና በፍቅር የሚከበር የአንድነት መገለጫ ነዉ

You are currently viewing መስቀል በአብሮነት፤ በመተሳሰብ እና በፍቅር የሚከበር የአንድነት መገለጫ ነዉ

AMN- መስከረም 16/2019 ዓ.ም

የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክቶ በመንበረረ ፓትርያሊክ በቅድስተ ቅዱሳን ማርየም ቤተክርስትያን የስብከተ ወንጌል መምህር ሀዋዝ ካሳዬ ከኤም ኤን ዲጂታል ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የዳመራ መነሻ ከጌታ መካነ መስቀል ፍለጋ ጋር የተያያዘ ታሪካዊ ዳራ እንዳለው ገልጸዋል።

መጋቤ ሐዲስ ሐዋዝ እንዳብራሩት፣ የጌታ መስቀል ከአይሁድ ጭቆና የተነሣ ተቀብሮ የቆየ ሲሆን፣ በወቅቱ በነበረው ተአምራት ምክንያት ጠላቶች ሊያጠፉት ሞክረው ነበር። የዳመራ በዓል መነሻም ይህንን የተቀበረ መስቀል ለማግኘት የተደረገው ጥረትና ታሪክ ነው።

በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ንግሥት እሌኒ (የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት) የተቀበረውን የጌታ መስቀል ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ማቅናቷን መምህር ሀዋዝ አንስተዋል። በወቅቱ በቦታው ሦስት ተራራዎች በመኖራቸው መስቀሉ የት እንደተቀበረ በቀላሉ ማግኘት አልተቻለም ነበር።

በመጨረሻም ችራኮስ በተባሉ የሀገር ሽማግሌ በተገኘ ጥቆማና ንግሥት እሌኒ ባደረገችው ጥልቅ ጸሎትና ሱባኤ መሠረት መልአኩ መመሪያ ሰጥቷል ይላሉ፡፡

የተቀበረበት ትክክለኛው ቦታ እንዲታወቅም ሕዝቡ እንጨት እንዲሰበስብ ተደርጎ ዳመራ እንዲለኮስ ተደረገ። በዳመራው ውስጥ የጨመረው የእጣን ጢስ ተነስቶ መስቀሉ ወዳለበት ቦታ አቅጣጫ በመስገዱና ምልክት በማሳየቱ ትክክለኛው ቦታ መታወቁን መምህር ሀዋዝ ገልጸዋል። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም «ሰገደ ጥስ» በማለት ይህንን ታሪክ መመስከሩን ጠቁመዋል።

ይህንን ተከትሎም በመስቀል ፍለጋው ቁፋሮ የተጀመረ ሲሆን፣ በመጋቢት 10 ቀን እውነተኛው የጌታ መስቀል ከድጓዱ ተገኝቶ እንዲወጣ መቻሉን መምህር ሀዋዝ ካሳዬ አስረድተዋል። የደመራም በዓል መነሻውና ትርጉሙ ከዚሁ የታሪክ ሂደት ጋር የተያያዘ መሆኑን አብራርተዋል።

በአሉ በሚከበርበት ወቅትም ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰዉ ልጆች የከፈለዉ መስዋዕትነት፤ ፍቅርና ዉለታ የሚታሰብበት መሆኑን በመግለጽ የእምነቱ ተከታዮችም ይህኑ ሃይማኖታዊ እሴት ጠብቀዉ ሊያከብሩ እንደሚገባም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review