AMN- መስከረም 16/2019 ዓ.ም
የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በላዛሪስት ጽዮን ማርያም ቁምስና እየተከበረ ነው፡፡
በቤተ-ክርስቲያኗ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንደራሴ አባ ተስፋዬ ወልደ ማርያምን ጨምሮ የቤተ-ክርስቲያኒቷ አባቶች፣ ዘማሪያን እና ምዕመናን በዓሉን ታድመዋል፡፡
በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አባ ተስፋዬ ወልደ ማርያም፤ መስቀል ሰማይና ምድር የታረቁበት፣ የፀብ ግርግዳ የፈረሰበት የፍቅርና የሰላም መሳሪያ መሆኑን ገልጸዋል።
መስቀል ትህትናን የሚያስተምር ስለመሆኑም አክለው ገልጸዋል።
በላይሁን ፍስሃ