የፌደራል መንግሥት ምስረታ …

AMN- መስከረም 24/2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ነገ የምትመሠርተው መንግሥት የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የታላቅ ሀገር ታሪካዊ ምዕራፍ እንደሆነ ይታመናል።

የአፍሪካ ሀገር በቀል እውቀቶች ፍልስፍና ተመራማሪ እና የአድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ቤኮ (ዶ/ር)፤ ነገ የሚካሄደውን የፌዴራል መንግሥት ምስረታ አስመልክቶ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ታላቅ ትሆናለች ብለዋል፡፡

የመንግሥት ምስረታ ህገ-መንግስሥታዊ እና ተቋማዊ ነው የሚሉት ዮሴፍ ቤኮ (ዶ/ር)፤ ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የህዝብ ድምጽ እየተከበረ መሆኑ በግልጽ እየታየ ነው ብለዋል፡፡

የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) ምክር ቤቶች በስኬት እንደተቋቋሙ፤ የክልል መንግሥታት እንደተመሰረቱ በመግለጽ የፌደራል መንግሥት ምስረታም ነገ እንደሚካሄድ አንስተዋል፡፡

ይህ ሂደት ኢትዮጵያ በህግ የበላይነት፣ በህዝብ ፈቃድና በህገ-መንግሥታዊ ስርዓት የምትመራ ሀገር መሆኗን ማረጋገጫ ነው ብለዋል።

ሜጋ ፕሮጀክቶችንና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን ማፋጠን የሚመሰረተው መንግስት ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች ተጠቃሽ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጰያውያን ከሀገር አልፎ ለዓለም ምሳሌ የሚሆን ስር የሰደዱ ችግሮችን እና አለመግባባቶችን በንግግር የሚፈቱባቸው እሴቶች አሉን ሲሉም አክለዋል፡፡

መንግሥት እንደ ሀገር ትልቅ የኢኮኖሚ መሰረት የሆኑ ዘርፎችን በተለይም የቱሪዝም መሰረተ ልማቶችን መገንባቱንም አንስተዋል፡፡

ተቋማት በቴክኖሎጂ እየታገዙ መሆኑን እንዲሁም የአዲስ አበባ ገጽታ መቀየሩንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review